Vendor Management Agreement

የበየነ መረብ (Internet) የገበያ ትስስር (“ስምምነት”) ገብቷል።

ስም እና አድራሻ ከዚህ በታች ያስገቡ

____________________________________________________

(በዚህ ስምምነት ውስጥ እንደ “አቅራቢው” ተጠቅሷል)

እና ፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች አ.ማ. አድራሻ:- ክልል፡ አዲስ አበባ ክ/ከተማ. ልደታ የቤት ቁጥር፡ 235

የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር፡ 0073022656

ስልክ ቁጥር: (+251) 946- 545454 /(+251) 943-566188

ኢሜል: info@kegeberew.com

(በዚህ ስምምነት ውስጥ “እኛ ፣ ወይም “የእኛ” ተብሎ ተጠቅሷል)።

ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ “Kegeberew.com” የተሰኘ የኢኮሜርስ ፕላትፎርም ባለቤት ነው።

Kegeberew Vendor Management (KVM) በርካታ አቅራቢዎችን በአንድ ቦታ የያዘ የበየነ መረብ (Internet) የገበያ ቦታ ነው (በአንድነት “KVM Platform” እየተባለ ይጠራል) ፣ በዚህም ሸማቾች የግብርና ምርቶችን፣ መጠጦችን፣ የቤት ዕቃዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ ግሮሰሪዎችን፣ ፈርኒቸሮችን፣ ተሽከርካሪዎችን እና ሌሎችን ከተሳታፊ አቅራቢዎች ማዘዝ እና መግዛት ይችላሉ።

ደንበኞች የአቅራቢዎችን ምርት ዝርዝር በKVM Platform ወይም 9858 የጥሪ ማእከል መስመር በመጠቀም ማዘዝ ይችላሉ።

የደንበኞች ትዕዛዝ በKVM ፕላትፎርም አማካኝነት ለአቅራቢዎች ወዲያውኑ ይደርሳል

የደንበኞችን ትዕዛዝ አቅራቢው ለደንበኞች ራሱ በሚያመቻቸው የማስረከቢያ መንገድ (Delivery arrangement) ማድረስ ወይም በእኛ አማካኝነት ማድረስ ይችላል።

የዚህ ስምምነት ተዋዋይ ወገኖች በሚከተለው ይስማማሉ፡

አንቀፅ 1፡ ሎጎ (አርማ) እና ሜኑ የመጠቀም ፍቃድ

1. ፐርፐዝብላክ ከዚህ ስምምነት ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ የአቅራቢውን ሜኑ እና ምርቶች በ kegeberew.com ላይ እንዲዘረዝር ፈቃድ አግኝቷል።

2. የኬቪኤም (KVM) ፕላትፎርም በዝርዝሮቹ ውስጥ የአቅራቢውን አርማ (ሎጎ) ወይም ሌሎች የማስተዋወቂያ ቁሳቁሶችን መጠቀም ይችላል።

3. የአቅራቢዎች ዝርዝር መረጃ በኬቪኤም (KVM) ፕላትፎርም አሁን ላይ ያለ ምንም ተጨማሪ ክፍያ ይለጠፋል ወደ ፊት ማስተካከያ ካለ የምናሳውቅ ይሆናል።

4. ከላይ በንዑስ አንቀፅ 3 የተገለፀው እንዳለ ሆኖ ፐርፐዝብላክ ለወደፊቱ ክፍያ ሊጠይቅ ይችላል

አንቀጽ 2፡ የአከፋፈል ሁኔታዎች

1. ትዕዛዞች ለደንበኞች ተደራሽ (Deliver) በሚደረጉበት ወቅት የእቃዎቹን ክፍያ ለ አቅርራቢው የምንከፈለው የእቃዎቹን ክፍያ ከደንበኛው ከተሰበሰበ በኋላ በ 24 ሰአት ውስጥ ይሆናል። ደንበኞቻችንን ቀጥታ በባንክ ወይም በሞባይል ባንኪንግ የክፍያ መንገዶች እናስከፍላለን።

2. ደንበኞች ለፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ከ2% – 10% (ሁለት በመቶ እስከ አስር በመቶ) የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ። የአገልግሎት ክፍያ መጠን በአንድ ሰው ትዕዛዝ እንደተደረገው የእቃዎች ዋጋ እና የትዕዛዝ መጠን የሚተገበር ይሆናል። የአገልግሎት ክፍያ ዝርዝር እንና መጠን ዋጋቸው ከዚህ ውል ጋር በቅጽ አባሪ ተደርጓል።

3. በአቅራቢዎች መቅረብ ያለባቸው እቃዎችን ኣቅራቢው በራሱ ሊያቀርብ ይችላል። በአቅራቢው የሚቀርቡ የንብረት ዓይነቶች ከዚህ ውል ጋር አባሪ ተደርገዋል

4. ከላይ በንዑስ አንቀፅ 3 በተገለፀው መሠረት አቅራቢው ንብረቶቹን ለደንበኛው ማቅረብ የሚችለው ደንበኛው ወደ ከገበሪው ዶት ኮም አካውንት ክፍያ ገቢ ካደረገ በኋላ ብቻ ነው። ይህንን ሳያደርጉ ትዕዛዝ ቢያስተናግዱ እኛ ሀላፊነት አንወስድም።

5. እኛ እና አቅራቢዎች የአገልግሎት ክፍያን እንዲሁም የአቅራቢው ሽያጭ ገቢ ክፍያን ለማስተካከል እና ለማስታረቅ የሚሰራ ቡድን ማቋቋም አለብን።

አንቀጽ 3፡ ውሉ የሚፀናበት ጊዜ

1. ይህ ውል ስምምነቱ ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ ለአሥራ ሁለት (12) ወራት የሚቆይ ይሆናል።

2. ሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች በዚህ ውስጥ ከተገለጹት ውሎች በመጣስ በሌላ ምክንያት ስምምነቱን ለማቆም ከፈለገ፣ የተጠቀሰው አካል ለሌላኛው ተዋዋይ ወገን የ15 የስራ ቀን የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ መስጠት አለበት።

አንቀጽ 4፡ የአቅራቢዎች ተግባራት እና ኃላፊነቶች

1. አቅራቢው ሁል ጊዜ ቢያንስ አንድ የስልክ መስመር በአቅራቢው የስራ ሰአት የሚሰራ ሊኖረው ይገባል፣ አቅራቢው ትእዛዝ ለመቀበል የሚያገለግለውን ‘ከገብሬው ፕላትፎርም’ ለመጫን ቢያንስ አንድ ስማርት (ዘመናዊ) ስልክ ማዘጋጀት አለበት።

2. አቅራቢው በKVM ፕላትፎርም ወይም 9858 የጥሪ ማዕከል ትዕዛዙን በተባለው ልክ ማዘጋጀት አለበት::

3. ትዕዛዙ ለአቅራቢው በደረስ 24 ሰዐት ባላነሰ ጊዜ ውስጥ ትዕዛዙ ለደንበኛው ዝግጁ መሆን አለበት።

4. አቅራቢው ደንበኛው ትዕዛዙን በሰጠ በአምስት ደቂቃ ውስጥ ለደንበኛው ትእዛዙን የመሰረዝ ወይም የመለወጥ ዕድል ሊሰጠው ይገባል።

5. አቅራቢው በ KVM Platform ላይ ያለው ዝርዝር ማለትም የዕቃዎቹ መገኛ አካባቢ፣ የስራ ሰዓት፣ የምርት ዝርዝሮች እና ዋጋን ጨምሮ ወቅታዊ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለበት። በእነዚህ ውስጥ ያሉ ማንኛውም ለውጦች በአንድ የስራ ቀን ውስጥ ለእኛ ማሳወቅ አለባቸው።

6. አቅራቢው በKVM ፕላትፎርም ላይ የዘረዘራቸውን ዕቃዎች ከጨረሰ ለፐርፐዝብላክ ማሳወቅ አለበት። ዕቃዎቹ ማለቃቸውን በጊዜ ሳያሳውቅ ቀርቶ ደንበኛ በእቃዎቹ ላይ ትእዛዙን ቢያስተላልፍ ደንበኛው ተጨማሪ ክፍያ ሳይከፍል መሰረዝ ይችላል

7. በዚህ ውል መሠረት የሚቀርቡት ሁሉም አቅርቦቶች ጥራት ያላቸው እና ምንም ግልጽ ወይም ጉልህ ጉድለት የሌላቸው እና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸውን አቅራቢው ዋስትና ይሰጣል።

አንቀጽ 5፡ ተግባሮቻችን እና ኃላፊነታችን

1. በእኛ “KVM” ፕላትፎርም ላይ ሁሉንም ተዛማጅ የአቅራቢ መረጃዎችን እንዘረዝራለን።

2. በሥራ ሰዓት አገልግሎት እና ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ እንሆናለን።

3. በአቅራቢው ዕቃዎች ላይ የተሰጡ ትዕዛዞችን እንደደረሰን እናስተላልፋለን እናረጋግጣለን።

4. በአቅራቢው ግብዓቶች እና ጥያቄዎች መሰረት የአቅራቢዎችን ዝርዝር በተመለከተ በእኛ “KVM” ፕላትፎም ላይ እቃዎችንና እና ሌሎች ዝርዝሮች ላይ ማሻሻያ እናደርጋለን

5. ቅሬታዎችን እና አስተያየቶችን ከደንበኞች ወደ ሻጮች እናስተላልፋለን እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የማስተካከያ እርምጃዎችን እንወስዳለን።

አንቀፅ 6: ተጠያቂነትን በሚመለከት

1. በአቅራቢው ምክንያት ለሚደርስ ማንኛውም ጉዳት እኛ ተጠያቂ አንሆንም

2. ጉዳቱ የተሳሳቱ ዝርዝሮች፣ የተጭበረበሩ ትዕዛዞች እና ሌሎች ጉዳቶችን ይጨምራል በዚህም ምክንያት የሚመጡ ኪሳራዎችን ይጨምራል።

3. አቅራቢው እኛን ከምርት ጥራት ጋር በተያያዘ ማንኛውም የይገባኛል ጥያቄዎች ፣ ኪሳራዎች ፣ ወጪዎች እና እዳዎች ነፃ ሊያደርገን ይገባል።

አንቀጽ 7፡ የውል እድሳት በሚመለከት

1. ይህ ስምምነት ከመጀመሪያው ቃል በኋላ ለአንድ (1) ዓመት ጊዜ ይታደሳል ከዚያ በኋላ ለእያንዳንዱ ተከታታይ ዓመት ቀጣይነት ያለምንም ተጨማረ ንግግር ይታደሳል።

2. አቅራቢው በፅሁፍ ካላሳወቀን በስተቀር ውሉ በራሱ ጊዜ የሚታደስ ይሆናል።

3. አቅራቢው ዕድሳት እንዲደረግ ካልፈለገ ቢያንስ የመጀመሪያው ውል ከማለቁ ከአርባ አምስት (45) ቀናት በፊት ለእኛ በፅሁፍ ማሳወቅ አለበት።

አንቀጽ 8፡ የግብይት ስምምነት (Marketing Agreement)

1. እኛ ለማስታወቂያ የምንጠቀምባቸውን ፍላየሮች ካርዶች ወዘተ… (እኛ የምናቀርባቸው) አቅራቢው በግልፅ በሚታይ ቦታ ማስቀመጥ ይኖርበታል። 2. በትዕዛዝ በሚወሰዱ ማንኛውም ምርቶች ውስጥ የከገበሬው ፕላትፎርምን የሚያስተዋውቁ ፍላየሮችን ወይም ካርዶች ከትዕዛዙ ጋር ጨምረው መላክ ይኖርባቸዋል።

3. የኛን አርማ ወይም አጭር የጥሪ ማዕከል ቁጥር በጥቅላቸው ወይም በሜኑ ላይ ያካትታሉ።

4. በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ ቻናሎቻችን ላይ በተከታታይ አቅራቢዎችን የማስተዋወቅ ስራ እንሰራለን።

አንቀጽ 9፡ የግብር አተገባበር

1. ሁለቱም ወገኖች በምርት ላይ ወይም በህግ የሚጣሉትን ማንኛውንም ግብር መክፈል አለባቸው።

አንቀጽ 10፡ የአስተዳደር ህግ

ይህ ስምምነት ትክክለኛነት፣ አተረጓጎም እና አፈፃፀሙን ጨምሮ በሁሉም ጉዳዮች ላይ በኢትዮጵያ ህግ መሰረት ይተረጎማል።

አንቀጽ 11፡ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

1. ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ የዚህን ስምምነት ድንጋጌዎች ከአስራ አምስት (15) የስራ ቀን በፊት ለአቅራቢው በፅሁፍ በመግለፅ ማሻሻል ይችላል።

2. ከላይ በንዑስ አንቀዕ አንድ በተደረገው ለውጥ አቅራቢው ካልተስማማ አስራ አምስት (15) የስራ ቀን ጊዜ ውስጥ ለፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ በሚሰጥ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ ይህንን ስምምነት ማቋረጥ ይችላል።

3. ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ይህንን ስምምነት አቅራቢው የአገልግሎቶቹን ጥራት ካልጠበቀ እና ከደንበኞች ቅሬታዎችን የማያስተናግድ ከሆነ አስራ አምስት የስራ ቀናት ማስጠንቀቂያ (15) በመስጠት የማቋረጥ መብት ይኖረዋል

4. ግጭት በሚፈጠርበት ጊዜ ሁለቱም ወገኖች በድርድር መፍትሄ ይሰጣሉ ።

5. ሁለቱም ወገኖች የዚህን ውል ሚስጥር ለመጠበቅ ተስማምተዋል።

አንቀጽ 12፡ የአገልግሎት ክፍያ በሚመለከት

የአገልግሎት ክፍያ ስሌት

1. የትህዛዙ ጠቅላላ መጠን <=5000 ብር ከ ከሆነ 10% የአገልግሎት ክፍያ እናስከፍላለን

2. የትህዛዙ ጠቅላላ መጠን >=5001 ብር እስከ <=10000 ብር ከ ከሆነ 8% የአገልግሎት ክፍያ እናስከፍላለን

3. የትህዛዙ ጠቅላላ መጠን >=10001 ብር እስከ <=15000 ብር ከ ከሆነ 6% የአገልግሎት ክፍያ እናስከፍላለን

4. የትህዛዙ ጠቅላላ መጠን >=15001 ብር እስከ <=20000 ብር ከ ከሆነ 4% የአገልግሎት ክፍያ እናስከፍላለን

5. የትህዛዙ ጠቅላላ መጠን >=20001 ብር እስከ <=40000 ብር ከ ከሆነ 3% የአገልግሎት ክፍያ እናስከፍላለን

6. የትህዛዙ ጠቅላላ መጠን >=40001 ብር ከ ከሆነ 2% የአገልግሎት ክፍያ እናስከፍላለን

አንቀጽ 13፡ ተፈጻሚነትን በሚመለከት

ይህ ስምምነት በሁለቱም ወገኖች ከተስማሙ እና ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ ተፈጻሚነት ይኖረዋል።

ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ በኩል በአቅራቢው በኩል

ስም __________________                                                                   ስም__________________

ፊርማ _________________                                                                  ፊርማ _________________

ቀን___________________

ቀን___________________

 

    0
    Your Cart
    Your cart is emptyReturn to Home