የከገበሬው ኢኮሜርስ ምርት አከፋፋዮች የውል ስምምነት

የከገበሬው ኢኮሜርስ ምርት አከፋፋዮች የውል ስምምነት

ፐርፐዝ ብላክ ኢቲኣኤች ..

አድራሻ:- ክልል፡ አዲስ አበባ  /ከተማ. ልደታ  የቤት ቁጥር፡ 235

የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር፡ 0073022656  ስልክ ቁጥር +(251) 946- 545454 /(+251) 943-566188

ኢሜል ceo@purposeblack.et

 (በዚህ ስምምነት ውስጥ ውል ሰጪ ተብሎ ተጠቅሷል)

(የድርድቱ ስም)

አድራሻ:- ክልል፡ ………. ከተማ:  ……………….  /ከተማ.…. የቤት ቁጥር፡

የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር፡ …….  ስልክ ቁጥር …….ኢሜል……

 (በዚህ ስምምነት ውስጥ ውል ተቀባይ ተብሎ ተጠቅሷል)

ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ (ውል ሰጪ) የአገልግሎት ተደራሽነቱን ለማስፋት ከነደፋቸው ስልቶች አንዱ ኑ አብርን እንስራ በሚለው መርሁ መሠረት የተለያዩ አካላትን ጋብዞ በጋራ መስራት ነው፡፡ በመሆኑም የምርት ስርጭት ስርዓቱን በማስፋት የአገልግሎት ተደራሽነቱን ሰፊ ለማድረግ አቅዷል፡፡ ይህንንም ለማረጋገጥ ብሄራዊ የምርት አካፋፋይ ህጋዊ ወኪሎችን በመቅጠር ማሰራትን ይፈልጋል፡፡

ይህ የውል ስምምንነት በኢትዮጵያ በየትኛውም አካባቢ የሚገኙና ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ (ውል ሰጪ) ምርቶች ሕጋዊ ወኪል አከፋፋይ ሆነው መስራት ለሚፈልጉ የንግድ ተቋማት ጋር ለመስራትና በህጋዊ ማዕቀፍ ለመደገፍ የተደረገ የውል ስምምነት ነው።

አንቀጽ አንድ

የውሉ ህጋዊ ሀይል

1.1. ይህ ውል በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1678/1731 እና 2005 ድንጋጌዎች መሰረት ተዋዋይ ወገኖች አውቀን፣ አምነንበትና ወደን በሙሉ ፈቃደኝነት ያደረግነውን ምርት አከፋፋዮች የውል ስምምነት ሲሆን ውሉ በእኛ በተዋዋዬች መካከል ሕግ ሆኖ ያገለግላል፡፡  የውሉ ሰነድም አስተማማኝና በቂ ማስረጃችን ነው፡፡

1.2. ውሉ በፍትሐብሔር ሕግ ስለውሎች በጠቅላላው በተፃፉት ድንጋጌዎች መሰረት የተቷቋመ ውል በመሆኑ በውሉ አተረጓጎም እና አፈፃፀም ላይ እነዚህ ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት አላቸው፡፡

አንቀፅ ሁለት

የውሉ ዓላማ

የዚህ ውል ዓላማ ውል ሰጪ ምርቶቹን በመላው ኢትዮጵያ ለማከፋፈል በመፈለጉ ከምርት አከፋፋይ ወኪሎች ጋር በህጋዊ መንገድ በጋራ ለመስራት በማሰብ ፍትሃዊ፣ ሊሰራ የሚችል እና በሁለቱም ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት ያለው የውል ስምምነት ነው።

አንቀፅ ሶስት

ትርጓሜ

በዚህ ውል መሰረት

3.1 ወኪል፡ ወኪል ማለት በፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ምርት የማከፋፈል ህጋዊ ስልጣን የተሰጠው ህጋዊ ሰውነት ያለው የንግድ ተቋም ማለት ነው፡፡

3.2 ምርት አከፋፋይ፡ ምርት አካፋፋይ ማለት በፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ የቀረበለትን የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች ካምፓኒው በሚያወጣለት የዋጋ ተመን መሠረት ለሸማቾች የሚሸጥ/የሚያከፋፍል ህጋዊ ወኪል ማለት ነው፡፡

3.3 ብሄራዊ፡ ብሄራዊ ማለት በኢትየጵያ በየትኛውም ቦታ የሚገኝ ማለት ነው፡፡

አንቀፅ አራት

የውል ሰጪው መብትና ግዴታ

4.1 ውል ሰጪው ምርቱን በታዘዘው የጥራት ልክና መጠን ለውል ተቀባይ ያደርሳል

4.2 ውል ሰጪው ትዕዛዙን በተባለው ፍጥነት ማድረስ ይኖርበታል

4.3 ውል ሰጪው ለሚያደርሳቸው ንብረቶች ወይም ምርቶች ክፍያ በማንኛውም ሁኔታ ቀድሞ ሊከፈለው ይገባል

አንቀፅ አምስት

የውል ተቀባይ መብትና ግዴታ

5.1 ውል ተቀባይ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የቲን ተመዝጋቢ መሆን ይኖርበታል

5.2 ውል ተቀባይ ቋሚ የንግድ ቦታ (ይህንን ማረጋገጫ የሚሆን የባለቤትነት ወይም የክራይ ውል መቅረብ ይኖርበታል)

5.3 ውል ተቀባይ የንግድ ቦታ ስፋት ቢያንስ 16 ካሬ ሜትር ሊኖረው ይገባል፡፡

5.4 ውል ተቀባይ በንግድ ቦታው ላይ በትክክል የሚሰራ ሚዛን እና ምርትን በአግባቡ ማስቀመጥ የሚያስችል በቂ ቦታ እና መደርደሪያ ሊኖረው ይገባል፡፡

5.5 ውል ተቀባይ ህጋዊ የሽያጭ ደረሰኝ መስጠት ይኖርበታል፡፡

አንቀፅ ስድስት

ትዕዛዝን በሚመለከት

6.1 የምርት ፍላጎት ትዕዛዛ መቅረብ ያለበት በውል ተቀባይ ሲሆን የሚቀርበውም የውል ሰጪ የጥሪ ማዕከል ስልኮችን በመጠቀም ወይም የከገበሬውን የኢኮሜርስ ዌብሳይት በመጠቀም ብቻ ይሆናል፡፡

6.2 ውል ሰጪው የምርት ፍላጎት ትዕዛዝ ለክፍለሃገር ወኪሎች ትዕዛዝ ባቀረቡ በ72 ሰዓት ውስጥ ለአዲስ አባባ ወኪሎች ትዕዛዝ ባቀረበ በ48 ሰዓት ውስጥ ትዕዛዛቸው የሚስተናግድ ይሆናል

አንቀፅ ሰባት

የትዕዛዝ መሠረዝን በሚመለከት

7.1 ውል ተቀባይ ደንበኞቹ ትዕዛዝን በሰረዙ በአንድ ሰዐት ውስጥ ለውል ሰጪ ማሳወቅ ይኖርበታል

7.2 ውል ተቀባይ የትዕዛዝ መሰረዝን ለውል ሰጪው ሳያሳውቅ የቀረ እንደሆነ ትዕዛዙን በሚመለከት መሉ ሀላፊነትን ይወስዳል

አንቀፅ ስምንት

የምርት ርክክብን በሚመለከት

8.1 ውል ሰጪው ምርት ለውል ተቀባይ የሚያቀርበው የራሱን ትራንስፖርት አገልግሎት በመጠቀም በአድራሻቻው ይሆናል፡፡

8.2 ውል ሰጪው እና በውል ተቀባይ መካለል ርክክብ የሚፈፀመው በህጋዊ የመረከቢያ ሰነድ ነው

8.3 ምርቶቹ ወደ ውል ተቀባይ (ወኪሎች) ከተላለፈ በኋላ ንብረቶቹ ባሉበት ደረጃ ሙሉ ሀላፊነት (Full liability) ወደ ውል ተቀባይ ይዞራል

8.4 ውል ተቀባይ በምርት መረከቢያ ሰነድ አማካኝነት የተረከቡትን ምርት በማንኛውም ምክንያት መመለስ አይችልም።

አንቀጽ አስር

ውሉ የሚቋረጥበት ምክንያት

10.1 ይህ ውል በሁለቱም ወገኖች በሁለቱ ወገኖች የጋራ ስምምነት ሊቋረጥ ይችላል፤

10.2 በኢትዮጰያ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1793 ከአቅም በላይ ተብሎ በተገለፀው ሁኔታ መሰረት ሊቋረጥ ይችላል

አንቀፅ አስራ አንድ

የአከፋፈል ሁኔታን በሚመለከት

11.1 ውል ተቀባዮች ለውል ሰጪ የምርቱን ክፍያ የሚከፍለው በባንክ በኩል ነው።

11.2 ውል ሰጪ የተሻለውን የሞባይል ባንኪንግ ሲስተም አወዳድሮ ክፍያ የሚፈፀምበትን የባንክ ዓይነት ለውል ተቀባይ ያሳውቃል።

11.3 ውል ተቀባይ ውል ሰጪው በሚያቀርበው የዋጋ ተመን መሰረት ምርቶቹን መሸጥ ይኖርበታል።

11.4 ውል ተቀባይ ለሸጠው ምርት 5% ኮሚሽን ይከፈለዋል።

አንቀፅ አስራ ሁለት

ግብርን በሚመለከት

12.1 ሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች በመንግስት የሚጣልባቸውን የየራሳቸውን ግብር ይከፍላሉ

12.2 ከኮሚሽን ክፍያ 2% ዊዝሆልዲንግ ታክስ ተቀናሽ ይሆናል

አንቀፅ አስራ ሶስት

አለመግባባትን መፍታትን በሚመለከት

13.1 ተዋዋይ ወገኖች በመካከላቸው ግጭት ወይንም አለመግባባት ሲከሰት በተቻለ መጠን በመግባባት በጋራ ችግሩን በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ለመፍታት ጥረት ማደረግ አለባቸው፡፡

13.2 ተዋዋይ ወገኖች በመካከላቸው የተፈጠረውን አለመግባባት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ መሠረት ለመፍታት ካልቻሉ ጉዳያቸውን ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡

አንቀጽ አስራ አራት

ተፈጻሚነት  ያላቸው  ሕጎች

ውሉን ሥራ ላይ ለማዋል ወይንም ለመተርጐም ባስፈለገ ጊዜ ሁሉ የኢትዮጵያ የውል ሕጐች በጠቅላላው እንዲሁም የአስተዳደር ውል በተለይ ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል፡፡

አንቀጽ አስራ አምስት

ውሉ የሚፀናበት ጊዜ

ይህ ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ በተዋዋይ ወገኖች እና በእነርሱ ወራሾች ወይም በተተኪዎቻቸው ላይ የሕግ ኃይል ኖሮት የፀና ይሆናል፡፡

ይህ ውል ዛሬ … ቀን 2015 ዓ.ም  በአዲስ አበባ ከተማ ተደረገ፡፡

ስለ ውል ሰጪ                                                                         ስለ ውል ተቀባይ

ስም ___________________________         ስም    _______________________

ፊርማ__________________________          ፊርማ   _______________________

    እማኞች/ምስክሮች

    1ኛ/   ስም _____________________            ፊርማ   ____________________

     2ኛ/   ስም _____________________           ፊርማ   _______________________

    0
    Your Cart
    Your cart is emptyReturn to Shop