Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop

ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ የከገበሬው ምርት ስርጭት ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር አካሄደ፡፡

በእለቱ የተገኙ በከገበሬው ምርት ስርጭት ፕሮጀክት የስራ ዕድል ያገኙ ወጣቶች

የከገበሬው ምርት ስርጭት ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር በኩባንያው ዋና መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር  ፍሰሀ እሸቱ እና ሌሎች የኩባንያው ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ጥቅምት 22 ቀን 2015ዓ.ም አከናውኗል፡፡
በመርሀ ግብሩ ንግግር ያደረጉት የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ እለቱ  ታሪካዊ እንደሆነ ገልጸው የጥቁር ህዝቦችን ታሪክ ዘላቂ በሆነ ኢኮኖሚያዊ እድገት ለመገንባት ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡አክለውም በከገበሬው ምርት ስርጭት ፕሮጀክት የስራ ዕድል ያገኙ ወጣቶች ከፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ጋር በጋራ በታማኝነት ከሰሩ እድገትን ማስመዝገብ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡
የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ዋና ዓላማ አብሮ በመስራት ድህነትን ታሪክ ማድረግ ነው ያሉት ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ ይህ በሚሆንበት ወቅትም አብረን በጋራ ማደግ እንደሚቻል ኩባንያው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ያከናወናቸው ተግባራት ማሳያ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ


በመጨረሻም የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ ሪቫን በመቁረጥ በይፋ የፕሮጀክቱን ሥራ ያስጀመሩ ሲሆን በእለቱ የተገኙት እንግዶችም ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ከገበሬው ቀጥታ ተረክቦ ከሚያመጣቸው የግብርና ምርቶች በተጨማሪ በኩባንያው እሴት ተጨምሮባቸው የተመረቱ እንደ ዳቦ፣ ሽሮ፣ በርበሬ እና ሌሎች የምግብ ውጤቶች ሸመታ ተካሄዷል፡፡
                                                                                                                                    
ሪፖርተር:- ህይወት ከሊል

This image has an empty alt attribute; its file name is IMG_20221102_084001_076-150x150.jpg

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop